Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ አልሸባብ በሶማሊያ ቪላ ሮዝ ሆቴል የፈጸመውን ጥቃት አወገዘች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ መንግስት የአልሸባብ ሽብር ቡድን በሶማሊያ ቪላ ሮዝ ሆቴል የፈጸመውን የፈሪ ጥቃት በጽኑ አውግዟል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ÷ አልሻባብ የሽብር ቡድን በትናንትናው ዕለት በሶማሊያ ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት አካባቢ በሚገኘው ቪላ ሮዝ ሆቴል የፈሪ ጥቃት መፈጸሙን አስታውሷል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስትም በጥቃቱ ለተጎዱ ቤተሰቦች እና ለሶማሊያ መንግስት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ከሶማሊያ መንግስት ጎን እንደሚቆም እና በቀጣይ የሽብር ቡድኑን ለመዋጋት በቅንጅት እና በትብብር እንደሚሰራም በመግለጫው አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.