Fana: At a Speed of Life!

 ብራዚል ጥሎ ማለፉን መቀላቀሏን አረጋገጠች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኳታር ዓለም ዋንጫ ብራዚል እና ስዊዘርላንድ ምሽት ላይ የምድብ ሁለት ጨዋታቸውን አካሂደዋል፡፡

በዚህም ብራዚል ስዊዘርላንድን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ በምድቡ ያላትን ነጥብ ወደ ስድስት ከፍ አድርጋለች፡፡

ውጤቱን ተከትሎም ከፈረንሳይ በመቀጠል ጥሎ ማለፉን የተቀላቀለች ሁለተኛ ሀገር መሆን ችላለች፡፡

የብራዚልን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ካሰሚሮ 83ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.