Fana: At a Speed of Life!

የአንጀት መቆጣት መንስዔ እና ምልክቶች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአንጀት መቆጣት (Inflammatory Bowel Disease) ለምግብ መፈጨት ሂደት የሚያገለግሉት የሆድ እና አንጀት ክፍል መቆጣት ወይም እብጠት መፍጠርን ያመላክታል።

ይህ ደግሞ የሆድ ሕመም፣ መቁሰልና የክብደት መቀነስን ያስከትላል።

እንደ ህክምና ባለሙያዎች ገለፃ ትክክለኛ መንስኤው ባይታውቅም የሰውነት በሽታ የመከላከል አቅም እየተዳከመ ሲመጣ በሽታው ጎልቶ ይታያል።

በተጨማሪም በሽታው ያለባቸው ወላጅ፣ ወንድም ፣ እህት ወይም ልጅ ያላቸው ሰዎች በበሽታው የመያዝ እድላቸው ከፍተኛ ነው።

ሲጋራ ማጨስ እና የህመም ማስታገሻ መድሃኒቶችም እንደ ምክንያት ይታያሉ።

የህመም ምልክቶቹ እንደ ቁስለቱ ደረጃና የሚከሰትበት ቦታ ቢለያዩም ተቅማጥ፣ ድካም፣ የሆድ ህመም እና ቁርጠት፣ የምግብ ፍላጎት መቀነስ፣ ክብደት መቀነስ እና ሰገራ ላይ ደም ማየት ይጠቀሳሉ፡፡

ከአንጀት መቆጣት ህመም  ጋር ተያይዞ የአይን መቆጣት ወይም ህመም፣ የቆዳ በሽታ፣ እና የመገጣጠምያ ህመምን ሊያስከትል እንደሚችል   ከጥቁር አንበሳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ገፅ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.