Fana: At a Speed of Life!

ያለውን መሬት ጥቅም ላይ ለማዋል በሚሠራው ሥራ ማህበረሰቡ ተባባሪ ሊሆን ይገባል- አቶ አወል አርባ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ያለውን መሬት ጥቅም ላይ ለማዋል በሚሠሩ ሥራዎች ማህበረሰቡ የመንግሥት አጋር በመሆን አጋርነቱን ሊያሳይ ይገባል ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ተናገሩ፡፡

ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ከዱብቲ ወረዳ ነዋሪዎች እና አመራሮች ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በእርሻ ልማት ዙሪያ የሚስተዋሉ ችግሮችን እና የልማት ሥራዎች ያሉበትን ሁኔታ በተመለከተ መክረዋል፡፡

አቶ አወል አርባ በውይይቱ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ በእርሻ ልማት በሚሠሩ ሥራዎች ላይ ማህበረሰቡ እንቅፋት ሊሆን አይገባም ማለታቸውን የርዕሰ መስተዳድር ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

አመራሩም ማህበረሰቡ ወደ እርሻ ልማት እንዲያተኩር ድጋፍ በማድረግ እንዲያበረታታ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በተጨማሪ በዱብቲ ወረዳ ያለውን ሰፊ መሬት በመጠቀም መንግሥት መሬቶቹ ለእርሻ እንዲውሉ የተለያዩ ሥራዎችን እየሠራ መሆኑን አስረድተዋል።

በመሆኑም ያለውን መሬት ጥቅም ላይ ለማዋል በሚሠሩ ሥራዎች ማህበረሰቡ የመንግሥት አጋር በመሆን በተለያዩ ሥራዎች በመሳተፍ አጋርነቱን ሊያሳይ ይገባልም ነው ያሉት።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.