Fana: At a Speed of Life!

ኮሚሽኑ በክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች ተጨባጭ መረጃዎችን ለማግኘት መስራቱን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ባለፉት ጊዜያት ከትግራይ ክልል በስተቀር በሁሉም ክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች በመገኘት ተጨባጭ መረጃዎችን ለማግኘት መስራቱን አስታውቋል፡፡

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን እስካሁን ያከናወናቸውን ተግባራት በተመለከተ የኮሚሽኑ አባል ኮሚሽነር ዮናስ አዳዬ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በመግለጫቸውም ኮሚሽኑ ከተቋቋመ ጀምሮ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ያከናወናቸውን ጉዳዮች አብራርተዋል።

በዚህም ባለፉት ጊዜያት ከትግራይ ክልል በስተቀር በሁሉም ክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች በመገኘት ተጨባጭ መረጃዎችን ለማግኘት መስራቱን ነው የገለጹት፡፡

እስካሁን ባለው ጊዜም የሰሜኑን ጦርነት ጨምሮ የተወሰኑ ችግሮች ቢያጋጥሙም የታቀዱ ስራዎችን ለማከናወን መሰራቱን አስረድተዋል፡፡

በለይኩን ዓለም

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.