Fana: At a Speed of Life!

በተለያዩ ሀገራት ይሰሩ የነበሩ ዲፕሎማቶች የጎርጎራ ገበታ ለሀገር ፕሮጀክትን እየጎበኙ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በተለያዩ ሀገራት ይሰሩ የነበሩ ዲፕሎማቶች በጎንደር ከተማ የተለያዩ የልማት ስራዎችን እየጎበኙ ነው፡፡
 
ዲፕሎማቶቹ አሁን ላይ የጎርጎራ ገበታ ለሀገር ፕሮጀክትን በመጎብኘት ላይ መሆናቸው ተገልጿል፡፡
 
በጎንደር በቆይታቸውም የተለያዩ የልማት ስራዎችን ጨምሮ የፋሲል ቤተመንግስት እና የሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክን እንደሚጎበኙ ይጠበቃል፡፡
 
በተለያዩ ሀገራት ይሰሩ የነበሩ እና ሰሞኑን በአፍሪካ የልህቀት ማዕከል ስልጠና ሲወስዱ የቆዩት ዲፕሎማቶቹ በዛሬው ዕለት ጎንደር ከተማ መግባታቸው ይታወሳል፡፡
 
ዲፕሎማቶቹ ጎንደር ሲደርሱም የከተማዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና ሌሎች የስራ ሃላፊዎች አቀባበል አደርገውላቸዋል።
 
በምናለ አየነው
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.