Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ ከዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ጋር በስልክ ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 19 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ጋር በትናንትናው ዕለት በስልክ ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም በአፍሪካ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል በሚያስፈልጉ ወሳኝ ድጋፎች ዙሪያ መምከራቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በፌስቡክ ገጻቸው ላይ ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ዶክተር ቴድሮስ እና የዓለም ጤና ድርጅት ሰራተኞችን በዚህ አስቸጋሪ ወቅት እያሳዩት ያለውን ብቁ የአመራር ክህሎት አድንቀዋል።

ከዚህ ባለፈም ከመላው ዓለም ጎን በአጋርነት በመቆማቸው እንዲሁም ለኢትዮጵያ ብሎም ለአፍሪካ ስለሚያደርጉት ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.