Fana: At a Speed of Life!

የተለያዩ ድርጅቶች የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ለመግታት ለተቋቋመው ኮሚቴ የተለያየ መጠን ያለው የገንዘብ ድጋፍ እያደረጉ ነው

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 19 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ ድርጅቶች ለኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ድንገተኛ ሁኔታ ዝግጅት የሚውል የተለያየ መጠን ያለው የገንዘብ ድጋፍ እያደረጉ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለኮቪድ 19 ድንገተኛ ሁኔታ ዝግጅት የሚውል ገንዘብ እና ሌሎች አቅርቦቶችን የሚያሰባስብ ብሔራዊ የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ማቋቋማቸው ይታወቃል።

ድንገተኛ ሁኔታ ዝግጅት የሚውል ገንዘብ እና ሌሎች አቅርቦቶችን ለማሰባሰብ የቀረበውን ሀገራዊ ጥሪ ተከትሎም የተለያዩ ድርጅቶች የተለያየ መጠን ያለው የገንዘብ ድጋፍ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል።

በዚህ መሰረትም የአዋሽ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀመንበር አምባሳደር ዶክተር ዲባባ አብደታ 10 ሚሊየን ብር ድጋፍ ለብሔራዊ የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴው የሀብት ማሰባሰብ ንኡስ ኮሚቴ ሰብሳቢ አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ አስረክበዋል።

በተመሳሳይ የአዲስ ኢንተርናሽናል ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ ኃይሉ ዓለሙም ባንኩ የለገሰውን 2 ሚሊየን ብር ለአምባሳደር ምስጋኑ አስረክበዋል።

እንዲሁም የእናት ባንክ የቦርድ ሊቀመንበር ሃና ጥላሁን ለኮቪድ19 ድንገተኛ ሁኔታ ዝግጅትና መከላከል ባንኩ የለገሰውን 2 ሚሊየን ብር ለብሔራዊ የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴው አስረክበዋል።

የኤንስሪ ኤች ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅት ባለቤት እና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሀይደር ከማል በበኩላቸው፥ 1 ሺህ 500 ጠርሙስ የንጽሕና መጠበቂያ ሳኒታይዘር ለሰላም ሚኒስቴር አስረክበዋል።

የዋን ውኃ አምራች የሆነው አባ ሐዋ ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅትም ለተመሳሳይ ዓላማ የሚውል የአንድ ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጉን ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.