Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን በኢጋድ ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ ካርቱም ገቡ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) 48ኛ መደበኛ ስብሰባ ለመሳተፍ ሱዳን ርዕሰ መዲና ካርቱም በዛሬው ዕለት ገብተዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ ካርቱም ሲደርሱ የሱዳን መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናትና የኢጋድ የስራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የሌሎች የኢጋድ አባል ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮችና የኢጋድ ዋና ፀሀፊ ወርቅነህ ገበየሁ ካርቱም ገብተዋል።

የኢጋድ ስብሰባ በወቅታዊ የአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና ፀጥታ፣ በግጭት እና በተፈጥሮ የደረሱ አደጋዎች እና ሰብአዊ እርዳታ፣ የምግብ ዋስትና እና በሌሎች ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች በአጀንዳነት ቀርበው ውይይት ይካሄድባቸዋል ተብሎ ይጠበቃል።

የኢጋድ ተቋማዊ ማሻሻያዎች የደረሰበት ሁኔታም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ይደረግበታል ተብሎ እንደሚጠበቅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.