Fana: At a Speed of Life!

በ2ኛው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም አፈጻጸም ላይ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የገንዘብ ሚኒስቴር ሁለተኛውን ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም ይበልጥ ውጤታማ ማድረግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከግብርና እና ማዕድን ሚኒስትሮች ጋር ውይይት አድርጓል፡፡

የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ እዮብ ተካልኝ ከግብርና ሚኒስትር ዑመር ሁሴን ጋር ባደረጉት ውይይት÷ ባለፋት ሶስት ዓመታት በግብርናው ዘርፍ በመስኖ ስንዴ ምርትና በአረንጓዴ አሻራ የተከናወኑ ውጤታማ ተግባራት በሌሎች ዋና የምርት ዓይነቶች ሊደገሙበት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡

በተጨማሪም የምግብ ዋስትና በሚረጋገጥበትና ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ ተጨማሪ የምርት ዓይነቶች በሚስፋፉበት ሁኔታ ላይ መወያየታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ዶክተር እዮብ ተካልኝ እና የማዕድን ሚኒስትር ኢንጅነር ታከለ ዑማ በበኩላቸው÷የማዕድን ዘርፉ የሀገሪቱ ኢንድስትሪ ምርት መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት በሚያበረክተው አስተዋጾ ኦ ላይ መክረዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም ዕሴት የተጨመረባቸው የማዕድን ምርቶች ለውጭ ገበያ በስፋት በሚቀርቡበት ሁኔታ ላይ ገንቢ ውይይት ማድረጋቸው ተገልጿል፡፡

ውይይቱ በመጀመሪያው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አፈፃፀም ወቅት በየዘርፉ የተመዘገቡ ውጤቶችን መቃኘት ታሳቢ ያደረገ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

እንዲሁም በአፈጻጸም ወቅት ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን በመለየት በቀጣዩ ዕቅድ ሊካተቱና ትኩረት ሊደረግባቸው በሚገቡ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑ ነው የተመላከተው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.