Fana: At a Speed of Life!

ቻይና ከሩሲያ ጋር በኃይል ዘርፍ ያላትን ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር ዝግጁ መሆኗን ገለጸች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና ከሩሲያ ጋር በኃይል ዘርፍ ያላትን ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር ዝግጁ መሆኗን ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ገለጹ፡፡

ፕሬዚዳንት ሺ 4ኛው የቻይና-ሩሲያ የኃይል ፎረምን አስመልከተው ባስተላለፉት መልዕክት÷ የኃይል ዘርፍ ትብብር ለሀገራቱ የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ መጠናከር የመሰረት ድንጋይ የሚጥል ነው ብለዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም ዓለም አቀፍ የኃይል ደህንነትን ለማስጠበቅ አዎንታዊ ሚና እንደሚጫወት ተናግረዋል።

ቻይና እና ሩሲያ ከተጋረጡባቸው የውጭ ስጋቶች እና ተግዳሮቶች አንጻር በኮሙኒኬሽን እና በሌሎች ዘርፎች ያላቸውን ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

ቻይና ከሩሲያ በኃይል ዘርፍ በትብብር ለመስራት ቁርጠኛ መሆኗን የገለጹት ፕሬዚዳንት ሺ፥ ለዓለም አቀፍ የኃይል ዘርፍ ደህንነት ሁሉም አካላት በቅንጅት ሊሰሩ እንደሚገባ መጠየቃቸውንም ሺንዋ ዘግቧል፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.