Fana: At a Speed of Life!

በዓለም በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች ቁጥር 28 ሺህ ደረሰ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 19 ፣ 2012( ኤፍ ቢ ሲ) በዓለም አቀፍ ደረጃ በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች  ቁጥር 28 ሺህ 717 መድረሱ ተገልጿል።

በቅርቡ በቻይና የተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ  አሁን ላይ የተለያዩ የዓለም ሀገራትን በማዳረስ  በርካታ ዜጎችን ለህልፈት እየዳረገ ይገኛል።

በአሁኑ ወቅት በቫይረሱ ህይወታቸው ካለፉ ሰዎች በተጨማሪ 615 ሺህ 520 የሚሆኑ ዜጎች በቫይረሱ መያዛቸውን ጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ አስታውቋል።

ከ30ሺህ በላይ አዳዲስ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች  በአሜሪካ፣ ጣልያን፣ ቻይና፣ ስፔን ፣ ጀርመን፣ ፈረንሳይና ኢራን  የሚገኙ መሆኑ ተነግሯል፡፡

እስካሁን ጣልያን በቫይረሱ ሳቢያ 9ሺህ 134 ዜጎቿን በሞት ስትነጠቅ ፥ስፔን ፣ ቻይና ፣ ኢራን እና ፈረንሳይ ደግሞ ከ1ሺ በላይ ዜጎቻቸውን በሞት ተነጥቀዋል ፡፡

በስፔን በኮቪድ-19 ምክንያት ባለፉት 24 ሰዓታት 832 ሰዎች መሞታቸውን ተከትሎ በአጠቃላይ የ5 ሺህ 134  ዜጎች ህይወት ሲያልፍ 72ሺህ 248 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተይዘዋል።

ሃገሪቱም ከጣሊያን ቀጥላ ክፉኛ በቫይረሱ የተጠቃች ሀገር ሆናለች።

በአፍሪካ በ46 ሀገራት ከ3 ሺህ 778  በላይ ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ፥ 109 የሚሆኑት ደግሞ ህይወታቸው አልፏል።

በሌላ በኩል በአለም አቀፍ ደረጃ ከ 135 ሺህ በላይ ሰዎች ከቫይረሱ ማገገማቸው ተመላክቷል።

ምንጭ÷ቢቢሲ እና ሲጂቲኤን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.