Fana: At a Speed of Life!

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ስልጠና ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ስልጠና ዛሬ በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ተጀምሯል።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ ስልጠናው ባለፈው አንድ ዓመት በነበረው የምክር ቤቱ የሥራ አፈፃፀም የታዩ የዕውቀትና ክህሎት ክፍተቶችን ለመሙላት ያስችላል ብለዋል፡፡

የመንግሥት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ እንደገለጹት÷ ስልጠናው የምክር ቤቱን የማስፈጸም አቅም ለማጎልበት የሚያግዝ፣ ባለፈው ዓመት የታዩ ክፍተቶችን ለመሙላት አባላቱ ተጨማሪ ዕውቀትና ክህሎት የሚያገኙበት ነው፡፡

ለአራት ቀናት የሚቆየው ስልጠና በአምስት ዐበይት ጉዳዮች ላይ ትኩረት እንደሚያደርግ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.