Fana: At a Speed of Life!

በዓለም ዋንጫ አፍሪካዊቷ  ሴኔጋል  እና ኔዘርላንድስ ጥሎ ማለፉን ተቀላቀሉ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኳታር ዓለም ዋንጫ ምሽት 12 ሰዓት ኔዘርላንድስ ከኳታር እንዲሁም ሴኔጋል ከኢኳዶር ጨዋታቸውን አድርገዋል፡፡

በጨዋታው አፍሪካዊቷ ሴኔጋል  ኢኳዶርን 2 ለ 1 አሸንፋለች፡፡

በተመሳሳይ ሰዓት በተደረገ ጨዋታ ደግሞ ኔዘርላንድስ ኳታርን 2 ለ 0 አሸንፋለች፡፡

በዚህም ሴኔጋል እና ኔዘርላንድስ ጥሎ ማለፉን መቀላቀላቸውን አረጋግጠዋል፡፡

በዓለም ዋንጫ ምሽት 4 ሰዓት የፖለቲካ ተቀናቃኞቹ ኢራን እና አሜሪካ ከ24 ዓመታት በኋላ የሚያደርጉት ጨዋታ በጉጉት ይጠበቃል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.