Fana: At a Speed of Life!

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ከ37 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከተለያዩ ተቋማት ጋር በመተባበር የሀገር መከላከያ ሰራዊትን ለማጠናከር 37 ሚሊየን 677 ሺህ 848 ብር ድጋፍ አስረክቧል፡፡

በርክክቡ ወቅት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ አቶ ታገሠ ጫፎ÷ምክር ቤቱ ለሀገር አለኝታ የሆነው መከላከያ ሰራዊት ጥሩ ቁመና እንዲኖረው የሚያስችሉ የሕግ ማሻሻያዎችን እያደረገ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

የሀገር መከላከያ ሰራዊት የሀገሪቱን ሉዓላዊነት ለማስከበር የህይወት መስዋዕት የሚከፍል የሁሉም ሕዝብ መሆኑን ጠቅሰው÷ ሰራዊቱን በሁሉም ዘርፍ ማጠናከር እና መደገፍ እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል፡፡

የሀገር መከላከያ ሚኒስትር ዴዔታ ወይዘሮ ማርታ ሎውጂ በበኩላቸው÷ ምክር ቤቱ የሀገር መከላከያ ሰራዊት እንዲጠናከር ላደረገው የገንዘብ ድጋፍ እና ከዚህ በፊትም ስለተደረጉ ዘርፈ-ብዙ ድጋፎች ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በተጨማሪም የሀገር መከላከያ ሰራዊቱ እንዲጠናከር በገንዘብ ሲደግፉ ለቆዩ ተቋማት እና ግለ-ሰቦች የእውቅና ሰርተፊኬት ሽልማት ተበርክቷል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.