Fana: At a Speed of Life!

የ17ኛው የኢንተርኔት አስተዳደር ጉባኤ ተሳታፊዎች የሳይንስ ሙዚየምን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በመዲናዋ እየተካሄደ በሚገኘው 17ኛው ዓለም አቀፍ የኢንተርኔት አስተዳደር ጉባኤ ተሳታፊ የሆነው የቱርክ  ልዑካን ቡድን አባላት በሳይንስ ሙዚየም  የቴክኖሎጂ ዐውደ ርዕይን ጎብኝቷል፡፡

በኢትዮጵያ የቱርክ አምባሳደር ያፕራክ አልፕ የተመራው የልዑካን ቡድን በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የበለፀጉ የተለያዩ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ውጤቶችን መመልከቱን ከኢኒስቲትዩቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የልዑካን ቡድኑ አባላት በሙዚየሙ የተመለከቱት የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ውጤቶች እየተካሄደ ካለው የኢንተርኔት አስተዳደር ጉባኤ ስኬት ጋር ተዳምሮ ኢትዮጵያን የፈጠራ እና ብዛት ያላቸው የቴክኖሎጂ ሁነቶች መዳረሻ የማድረግ አቅም እንዳለው አመላክተዋል፡፡

የ17ኛው የኢንተርኔት አስተዳደር ጉባኤ በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት በአዲስ አበባ እየተካሄደ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.