Fana: At a Speed of Life!

የኢንተርኔት አስተዳደር ጉባኤ አዲስ አበባን ” ስማርት ሲቲ “ለማድረግ በምናደርገው ጥረት ላይ ተጨማሪ አቅም ይፈጥራል – ከንቲባ አዳነች

አዲስ አበባ፣ ህዳር 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የ17ኛው የኢንተርኔት አስተዳደር ጉባኤ አዲስ አበባን “ስማርት ሲቲ” ለማድረግ በምናደርገው ጥረት ላይ ተጨማሪ አቅም የሚፈጥርልን ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ፡፡

ከተማ አስተዳደሩ ዛሬ በአዲስ አበባ መካሄድ  በጀመረው 17ኛው ዓለም አቀፍ የኢንተርኔት አሰተዳደር ጉባዔ  ተሳታፊ ለሆኑ እንግዶች የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል አድርጓል።

ይህን አስመልክቶ ከንቲባ አዳነች በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው÷መዲናችን በርካታ አለምአቀፍ ሁነቶችን፣  ኮንፈረንሶችንና ሲፖዝየሞችን ለመታደም ከመላው አለም ለሚመጡ እንግዶቿ  በኢትዮጵያዊ ባህል ተቀብላና አስተናግዳ እየሸኘች ያለች የአፍሪካውያን ኩራት እና ድምቀት መሆን የቻለች ነች ብለዋል።

የዚህ ጉባኤ ዋና አጀንዳም የመላው አለም የኢንተርኔት አስተዳደር ጉዳይ የከተማችንም ቀዳሚ አጀንዳ ነው ያሉት ከንቲባዋ፥ በመሆኑም ጉባኤው  በተለይም  አዲስ አበባን “ስማርት ሲቲ” ለማድረግ በምናደርገው ጥረት ላይ ተጨማሪ አቅም የሚፈጥርልን ይሆናል ሲሉም ገልፀዋል፡፡

ለመላው የጉባኤ ተሳታፊ እንግዶችም” እንኳን ወደ ከተማችን በሰላም መጣችሁ  ያሉ ሲሆን÷ እንግዶቹ  መልካም ቆይታ እንዲሆንላቸውም  ተመኝተዋል፡፡

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.