Fana: At a Speed of Life!

ፈረንሳይ ለደሴ ሪፈራል ሆስፒታል 9 ሚሊየን ብር የሚያወጣ የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የፈረንሳይ ኤምባሲ ለደሴ ሪፈራል ሆስፒታል ዘጠኝ ሚሊየን ብር የሚያወጣ የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል፡፡
 
በኢትዮጵያ ፈረንሳይ አምባሳደር ሬሚ ማሪሾ እና የተለያዩ ሚኒስትሮች ለስራ ጉብኝት በዛሬው ዕለት ደሴ ከተማ ገብተዋል፡፡
 
አምባሳደር ሬሚ ማሪሾ ለደሴ ሪፈራል ሆስፒታል 9 ሚሊየን ብር የሚያወጣ የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አስረክበዋል፡፡
 
በሌላ በኩል የደሴ ሪፈራል ሆስፒታልን መልሶ መገንባት የሚያስችል አዲስ ፕሮጀክት ይፋ መደረጉ ተገልጿል፡፡
 
በጉብኝት መርሐ ግብሩ ሮላንድ ኮቢያን የአውሮፓ ህብረት ልዑክ የኢትዮጵያ ጽህፈት ቤት አምባሳደር ተወካይም ተገኝተዋል፡፡
 
 
በኢሳያስ ገላው
 
 
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.