Fana: At a Speed of Life!

የ16ኛው የአፍሪካ ወጣቶች ወር የማጠቃለያ ፕሮግራም እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የ16ኛው የአፍሪካ ወጣቶች ወር የማጠቃለያ ፕሮግራም በድሬዳዋ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

16ኛው የአፍሪካ ወጣቶች ወር “የወጣቶች ንቁ ተሳትፎና ተካታችነት ለስብዕና ልማት”በሚል መሪ ቃለ ለአንድ ወር ያህል በተለያዩ ክልሎች ሲከበር ቆይቷል፡፡

በአከባበሩ አደንዛዥ ዕፅ በወጣቶች ስብእና ላይ የሚያስከትለውን ተፅእኖ በተመለከተ ጠቃሚ መረጃዎች ሲተላለፉ መቆየታቸው ተገልጿል፡፡

ይሄው የአፍሪካ ወጣቶች ወር የማጠቃለያ ፕሮግራም በአሁኑ ሰዓት በድሬዳዋ ከተማ በደማቅ ዝግጅት እየተከበረ ይገኛል፡፡

በአከባበሩ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ፣ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ፣ ሚኒስትር ዴኤታዎችና ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች መገኘታቸውን ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.