Fana: At a Speed of Life!

የቅርንፉድ የጤና ጥቅሞች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ቅርንፉድ ጣፋጭ እና ጥሩ መዓዛ ያለው ቅመም ሲሆን በይበልጥ የሚታወቀው ለምግብ ማጣፈጫ ቅመምነት ሲውል ነው ፡፡

ሆኖም ግን በአንዳንድ ሀገራት በባህላዊ መድሃኒትነትም ጥቅም ላይ ይውላል፡፡

ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ቅርንፉድ የተለያዩ የጤና ጥቅሞች ያሉት ሲሆን በውስጡ የሚገኙት ውህዶች የጉበት ጤናን ለመጠበቅ እና የደም ስኳር መጠን እንዲስተካከል ማድረግን ጨምሮ በርካታ የጤና ጥቅሞች አሉት፡፡

ከእነዚህም ውስጥ

1.ቅርንፉድ በውስጡ ካርቦ ሃይድሬት ፣ አሰር (ፋይበር)፣ ካሎሪ፣ ማንጋነዝ፣ ቫይታሚን -ኬ የተባሉ ቫይታሚን እና ሚኒራሎችን የያዘ ሲሆን በተለይ ማንጋነዝ የአንጎል ተግባርን የማስጠበቅ እና ጠንካራ አጥንት እንዲኖር ያስችላል፡፡

2. በፀረ-አንቲኦክሲዳንት የበለፀገ ሲሆን ጭንቀትን ለመቀነስ ይረዳል፤

3. ጥናቶችእንደሚያሳዩት በቅርንፉድ ውስጥ የሚገኙት ውህዶች የካንሰር ሕዋሳትን እድገት እንደሚቀንስ እና የካንሰር ሕዋሳትን እንደሚገድል ፍንጭ የተገኘ ሲሆን እርግጠኛ ለመሆን ግን ተጨማሪ ምርምር እንደሚፈልግ ገልጸዋል፡፡

4. እንደ ባክቴሪያ ያሉ ረቂቅ ተሕዋስያን እድገትን ለማስቆም ይረዳል፤

5.የአጥንት ጤንነትን ለመጠበቅ ይረዳል፤

6.የጨጓራ አልሰርን ለመከላከል ፥ ቅርንፉድ ከላይ የተዘረዘሩ በርካታ አስገራሚ የጤና በረከቶች እና ተጨማሪ ጥናት የሚጠይቁ ሌሎች የጤና ጥቅሞች እንዳሉትም የጤና እና ሥነ ምግብ ባለሙያዎች ይናገራሉ።

ይህን የቅመም አይነት ከተለያዩ ጤናማ ምግቦች ጋር አዋህዶ መመገብ መልካም እንደሆነ ጥናቶች ያስረዳሉ፡፡

በተጨማሪም ከ5 እስከ 10 ደቂቃ በውሃ ውስጥ በማፍላት ከሻይ ጋር ሊወሰድ ይችላል፡፡

ምንጭ÷ኸልዝ ላይን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.