Fana: At a Speed of Life!

ሌቦችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል- አቶ ደስታ ሌዳሞ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በክልሉ ሌቦችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ ተናገሩ፡፡

በአሁኑ ወቅት ስር የሰደደውን ሌብነት ለመቆጣጠር ሙስናን የሚፀየፍ ማህበረሰብ መፍጠር ላይ በዋናነት መሥራት እንደሚገባም በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡

“ሙስናን መታገል በተግባር” በሚል መሪ ሐሳብ የተከበረው 19ኛው ዓለም አቀፍ የፀረ ሙስና ቀን የማጠቃለያ መድረክ በአለታ ወንዶ ከተማ ተካሂዷል፡፡

አቶ ደስታ ሌዳሞ በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ሌብነትና ብልሹ አሠራር የሕዝቦችን ፍትሐዊ ተጠቃሚነት የሚያዛባ ተግባር ነው ብለዋል፡፡

በግልም ሆነ በቡድን የሚፈጸም ሌብነት የሀገራችንን ኢኮኖሚ ከማቀጨጭ ባሻገር ዴሞክራሲ እንዳይበለጽግ፣ የአገር ሰላምና ፀጥታ እንዳይረጋገጥ ያደርጋል ነው ያሉት፡፡

በአሁኑ ወቅት ስር የሰደደውን ሌብነት ለመቆጣጠር ሙስናን የሚፀየፍ ማህበረሰብ መፍጠር ላይ በዋናነት መሥራት እንደሚገባም ገልጸዋል፡፡

ችግሩን ለመቅረፍ እና የሕዝቡን ፍትሐዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በቴክኖሎጂ የታገዘ ሥራ እንደሚከናወን ገልጸው÷ሌቦችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

የክልሉ የስነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ዘላለም ለማ እንደገለጹት÷ ሌብነትና ብልሹ አሠራርን ከስሩ ለመንቀል ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ይሠራል፡፡

በቢቂላ ቱፋ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.