Fana: At a Speed of Life!

የቀድሞው የቻይና ፕሬዚዳንት ጂያንግ ዜሚን ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞው የቻይና ፕሬዚዳንት ጂያንግ ዜሚን በ96 ዓመታቸው በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡

ጂያንግ ዜሚን ከደም ካንሰር ጋር በተያያዘ በተለያዩ የሰውነት ክፍሎቻቸው ላይ በደረሰባቸው ፅኑ ሕመም ምክንያት ሕይወታቸው ማለፉን የቻይና ብሔራዊ መገናኛ ብዙኃን ዘግቧል።

ጂያንግ ዜሚን ከፈረንጆቹ 1989 እስከ 2002 የቻይና ኮሙኒስት ፓርቲ ዋና ፀሃፊ እና ከፈረንጆቹ 1989 እስከ 2004 ደግሞ የማዕከላዊ ወታደራዊ ኮሚሽን ሊቀመንበር በመሆን አገልግለዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም ከፈረንጆቹ 1993 እስከ 2003 የቻይና ፕሬዚዳንት በመሆን ሀገራቸውን እንዳገለገሉ የሕይወት ታሪካቸው ያስረዳል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.