Fana: At a Speed of Life!

ክርስቲያኖ ሮናልዶ የሳዑዲውን ክለብ አል ናስር ለመቀላቀል መስማማቱ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ፖርቹጋላዊው አጥቂ ክርስቲያኖ ሮናልዶ የሳዑዲውን ክለብ አል ናስር ለመቀላቀል መስማማቱን ሚዲያዎች እየዘገቡ ነው፡፡

እንደ ሚረር እና ደይሊ ሜይል ዘገባ ሮናልዶ በአመት 173 ሚሊየን ዩሮ ይከፈለዋል የተባለ ሲሆን ይህም ሮናልዶን የዓለማችን ውዱ ተከፋይ ያደርገዋል።

ሮናልዶ ከፔርስ ሞርጋን ጋር ካደረገው አወዛጋቢ ቃለ ምልልስ በኋላ ከክለቡ ማንቼስተር ዩናይትድ ጋር ተለያይቷል።

የክርስቲያኖ ሮናልዶ ወኪል ጆርጌ ሜንዴዝ ቀደም ሲል ሮናልዶ አልናስርን እንዲቀላቀል ጥያቄ አቅርቦ የነበረ ሲሆን አሁን ላይ በወጡ መረጃዎች አልናስር በሮናልዶ ዝውውር መስማማቱ ተገልጿል፡፡

ማርካን ጠቅሶ ደይሊ ሜይል እንደዘገበው የ37 አመቱ ሮናልዶ ከክለቡ ጋር ለሁለት አመት ተኩል ለመጫዎት ተስማምቷል፡፡

የአምስት ጊዜ የባሎን ደ ኦር አሸናፊው ክርስቲያኖ ሮናልዶ በ118 ጎሎችን የፖርቹጋል የምንጊዜም ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ ነው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.