Fana: At a Speed of Life!

በማቻክል ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ5 ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በምዕራብ ጎጃም ዞን ማቻክል ወረዳ አማኑኤል ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የአምስት ሰዎች ሕይወት አልፏል፡፡

ከደብረ ማርቆስ አቅጣጫ ወደ ደንበጫ ይጓዝ የነበር አይሱዙ ተሽከርካሪ በአማኑኤል ከተማ አስተዳደር ልዩ ቦታው ጎጃም ዱር በተባለ አካበቢ ከባጃጅ ጋር በፈጠረው ግጭት ነው አደጋው የደረሰው፡፡

ከቀኑ 8 ሰዓት አካባቢ በተከሰተው በዚህ አደጋ የአምስት ሰዎች ሕይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ÷ በተወሰኑ ሰዎች ላይም የአካል ጉዳት መድረሱን ከማቻክል ወረዳ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.