Fana: At a Speed of Life!

1 ሺህ 85 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 21 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶስት ዙር በተከናወነ በረራ በሳዑዲ አረቢያ በችግር ያሉ ዜጎችን የመመለስ ስራ 1 ሺህ 85 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መመለስ ተችሏል።

ከተመለሱት ዜጎች መካከል 666 ወንዶች፣ 303 ሴቶች እና 116 ህፃናትና እድሜያቸው ከ18 አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ናቸው፡፡

ለተመላሽ ዜጎች ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማእከላት እንዲሄዱ መደረጉን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

ከሕዳር 12 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን በተከናወነ ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ 5 ሺህ 667 ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል፡፡

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.