Fana: At a Speed of Life!

48ኛው የኢጋድ የሚኒስትሮች መደበኛ ስብሰባ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 21 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሱዳን ርዕሰ መዲና ካርቱም የተካሄደው 48ኛው የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) የሚኒስትሮች መደበኛ ስብሰባ የኢጋድ ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ ያቀረቡትን ሪፖርት በማፅደቅ ተጠናቋል።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ኢጋድ በቀጣናው ያለውን የሰላም እና ፀጥታ እንዲሁም በሰብአዊ ጉዳዮች ዙሪያ ያጋጠሙ ችግሮችን ለመፍታት የተጓዘበትን ሂደት አድንቋል።

ምክር ቤቱ ኢጋድ በኢትዮጵያ በሰሜኑ ክፍል የተፈጠረውን ግጭት በሰላም ለመፍታት በተደረገው ሂደት እና በተፈረመው የሰላም ስምምነት ላይ የነበረውን ሚናም አድንቋል።

ሚኒስትሮች ኢጋድ ባቀረበው የሰዎች ነጻ እንቅስቃሴ በተመለከተ ሁለት ፕሮቶኮሎች መፈረማቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።

በስብሰባው ማጠቃለያ ላይ ባወጡት የጋራ መግለጫ ኢጋድ እያደረገ ላለው ተቋማዊ ማሻሻያ አባል ሀገራት የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.