Fana: At a Speed of Life!

የከተማ አስተዳደሩ በኦሪጎን የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውጤት ላስመዘገቡ አትሌቶች የመሬት ካርታ አስረከበ

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 21 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በኦሪጎን የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውጤት ላስመዘገቡ አትሌቶች የመሬት ካርታ አስረከበ።

የመሬት ካርታው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስረክበዋል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ሽልማቱ እና ህዝቡ ለስፖርቱ ያለው ፍቅርና ድጋፍ አትሌቶቹ የበለጠ ድልና ውጤት እንዲያስመዘግቡ የሞራል ስንቅ እንደሚሆናቸው እምነታቸው መሆኑን አስታወቀዋል።

አያይዘውም በስይን ቫሌንሺያ በማራቶን ውድድር የሚካፈለው የአትሌቲክስ ቡድን ኢትዮጵያን በዓለም አደባባይ ዳግም ከፍ እንዲያደርጉና ትልቅ ውጤት እንዲያስመዘግቡ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.