Fana: At a Speed of Life!

በዛሬው የዓለም ዋንጫ ጀርመን ከኮስታሪካ የምታደርገው ጨዋታ ይጠበቃል

 

አዲስ አበበ፣ ሕዳር 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ22ኛው የኳታር ዓለም ዋንጫ ዛሬ ከምድብ አምስት እና ስድስት ወደ ጥሎ ማለፉ የሚቀላቀሉ ቡድኖችን የሚለዩ ጨዋታዎች ይከናወናሉ፡፡

በዚህም መሰረት በምድብ አምስት ጀርመን ከኮስታሪካ ምሽት አራት ሰዓት ላይ የሚደርጉት ጨዋታ ከወዲሁ ትልቅ ግምት ተሰጥቶታል፡፡

በተመሳሳይ ሰዓት በዚሁ ምድብ ጃፓን ከስፔን ጨዋታቸውን የሚያከናውኑ ይሆናል፡፡

ስፔን 4 ነጥብ በመያዝ የምድቡ ቀዳሚ ስትሆን ÷ ጃፓን እና ኮስታሪካ ደግሞ እኩል ሶስት ነጥብ አላቸው፡፡

በምድቡ 1 ነጥብ በመያዝ ግርጌ ላይ የተቀመጠችው ጀርመን የዓለም ዋንጫ ቆይታዋን የሚወስነውን ተጠባቂ ጨዋታ ከኮስታሪካ ጋር የምታደርግ ይሆናል፡፡

በምድብ ስድስት ካናዳ ከወዲሁ መውደቋን ያረጋገጠች ቢሆንም የመርሐ ግብሯን ማሟያ ከሞሮኮ ጋር ምሽት 12 ሰዓት ላይ ታደርጋለች፡፡

በተመሳሳይ ምድብ እና ሰዓት ክሮሺያ እና ቤልጂዬም የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡

በ22ኛው የዓለም ዋንጫ እስካሁን በተካሄዱ መርሐ ግብሮች ስምንት ቡድኖች ጥሎ ማለፉን መቀላቀላቸውን አረጋግጠዋል፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.