Fana: At a Speed of Life!

የበይነ መረብ አስተዳደር ጉባዔን አፍሪካዊ አጀንዳ እንዲይዝ ማድረግ ተችሏል – ሁሪያ አሊ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የበይነ መረብ አስተዳደር ጉባዔን አፍሪካዊ አጀንዳ እንዲይዝ ማድረግ መቻሉን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴዔታ ሁሪያ አሊ ገለጹ።

የኢንተርኔት አባት በመባል በሚታወቁት ቬንት ሰርፍ ሰብሳቢነት የሚመራው የበይነ መረብ አስተዳደር የከፍተኛ መሪዎች ፓናል ውይይት ተካሂዷል።

በውይይቱ ሚኒስትር ዴዔታ ሁሪያ አሊ÷ጉባዔው የአፍሪካውያን ችግር የሆነውን የበይነ-መረብ ተደራሽነትን ችግር መፍታት አጀንዳ እንዲሆን መደረጉ እንዳስደሰታቸው ተናግረዋል።

ጉባዔው ለኢትዮጵያ ዘረፈ ብዙ ልምድ እንድታገኝ አስችሏል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ÷ በበይነ-መረብ ያልተገናኙነትን ማገናኘት ላይ በቀጣይም ትኩረት መደረግ እንዳለበት ጠቅሰዋል።

የበይነ መረብ አስተዳደር ጉባዔ ከፍተኛ የመሪዎች ጉባዔ ሰብሳቢ ቬንት ሰርፍ÷ በዳታ ጥበቃ ውስጥ ተጠያቂነትን ማስፈን እና ዓለም አቀፍ ትብብር ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።

በአዲስ አበባ እየተካሄደ ያለው 17ኛው የበየነመረብ አስተዳደር ጉባኤ እንደቀጠለ መሆኑን ከአይ ጂ ኤፍ ኢትዮጵያ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.