Fana: At a Speed of Life!

የትግራይ ታጣቂዎች ትጥቅ የሚፈቱበትን ዝርዝር ዕቅድ የሚሠራው የባለሞያዎች የጋራ ኮሚቴ ሽረ ላይ እየመከረ ነው – የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የትግራይ ታጣቂዎች ትጥቅ የሚፈቱበትን ዝርዝር ዕቅድ የሚሠራው የባለሞያዎች የጋራ ኮሚቴ ሽረ ላይ እየመከረ መሆኑን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።

አገልግሎቱ በሰጠው ወቅታዊ መረጃ፥ በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መሠረት ሕወሓት ትጥቅ የሚፈታበትን ዝርዝር ዕቅድ የሚያዘጋጀው የባለሞያዎች የጋራ ኮሚቴ ከትናንት ሕዳር 21 ቀንጀምሮ ሽረ ላይ ሥራውን መጀመሩን አመልክቷል።

ከፌዴራል መንግሥትና ከትግራይ ታጣቂዎች የተውጣጣው የባለሞያዎች የጋራ ኮሚቴ በቀጣይ ጥቂት ቀናት ሥራውን ያጠናቅቃል ተብሎ ይታመናልም ነው ያለው።

ኮሚቴው የሚያወጣው ዝርዝር ዕቅድ ትጥቅ የማስፈታት፣ ካምፕ የማስገባትና ተያያዥ ጉዳዮችን የሚመልስ ይሆናልም ብሏል።

ዝርዝር ዕቅዱን የማውጣት ተግባሩ፣ በቴክኒክ ጉዳዮች ምክንያትመዘግየቱ እንደሚታወቅ ነው ያመለከተው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.