Fana: At a Speed of Life!

የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተናን በኦንላይን ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ነው- ትምህርት ሚኒስቴር

አዲስ አበበ፣ ሕዳር 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተናን በኦንላይን ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የመውጫ ፈተናው መደበኛና መደበኛ ባልሆኑ ሁሉም መርሐ ግብሮች የሚመረቁ ተማሪዎችን እንደሚመለከትም ተመላክቷል፡፡

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ሳሙኤል ክፍሌ በመውጫ ፈተና ዙሪያ ለመንግስትና ለግል ዩኒቨርሲቲዎች በተዘጋጀ የምክክር መድረክ ላይ እንደገለጹት ÷ የመውጫ ፈተናው በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች በቀን፣ በማታና በርቀት መርሐ ግብር ለሚመረቁ ተማሪዎች ይሰጣል።

ከዚህ ዓመት ጀምሮ በመንግሥትና በግል ዩኒቨርሲቲዎች ተግባራዊ የሚደረገውን የመውጫ ፈተና በኦንላይን ለመስጠት እየተሠራ መሆኑንም ጠቁመዋል።
በመሆኑም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመሠረተ ልማት አቅሞቻቸውን ከወዲሁ በማረጋገጥ ለፈተናው ተገቢውን ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስበዋል።

የከፍተኛ ትምህርት አካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ዶክተር ኤባ በበኩላቸው ÷የመውጫ ፈተና የትምህርት ጥራትን ከማስጠበቅ ባሻገር የተማሪዎችንና የተቋማቱን ብቃት ለማሳደግ እንደሚያስችል መጠቆማቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.