Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ በሚገኙ 13 ዋና ዋና መንገዶች ላይ የፀረ ተዋህስ መድሃኒት ርጭት ተከናወነ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 20 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ በሚገኙ 13 ዋና ዋና መንገዶች ላይ የፀረ ተዋህስ መድሃኒት ርጭት ስራ ተከናወነ፡፡
 
የፀረ ተሃዋሲያን ርጭት ተግባሩ ዋና ዋና መንገዶችን ከተሃዋስያን ነፃ ከማድረግ ባለፈ የከተማው ነዋሪዎች ለሁኔታው አሳሳቢነት ትኩረት እንዲሰጡና ራሳቸውን እንዲጠብቁ ግንዛቤ ለማሳደግ የሚደርገው ጥረት አካል እንደሆነ ኢ/ር ታከለ ኡማ በፌስቡክ ገፃቸው ተናግረዋል።
 
የፀረ – በሽታ አምጭ ተዋህስ መድሀኒት ርጭት የሚካሄድባቸው መንገዶች 41 ኪሎ ሜትር የሚሽፍኑ ናቸው።
 
ከመስቀል አደባባይ – ቦሌ ፣ -ከመስቀል አደባባይ – ጦር ሃይሎች ፣ – ከመስቀል አደባባይ – 6 ኪሎ ፣ -ከመስቀል አደባባይ – ጎተራ – ሳሪስ -ከመስቀል አደባባይ – መገናኛ ፣ -ከብሄራዊ – ሜክሲኮ፣ -ከሱፐር ማርኬት – ካዛንችስ – ኡራዔል ፣ – ከምኒልክ አደባባይ – አምባሳደር – መስቀል አደባባይ፣ – ከምኒልክ አደባባይ – ፓስተር፣ – ከምኒልክ አደባባይ – 4 ኪሎ – መገናኛ፣ ከምኒልክ አደባባይ – 6 ኪሎ ፣ – ከምኒልክ አደባባይ – አውቶብስ ተራ ፣ – ከምኒልክ አደባባይ – ተክለሃይማኖት ርጭት የተከናወነባቸው አካባቢዎች ናቸው።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.