Fana: At a Speed of Life!

ክፍለ ከተማው ለ65 ኢንተርፕራይዞች የመስሪያ ቦታ ሼድ ቁልፍ አስረከበ

አዲስ አበበ፣ ሕዳር 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ለ65 ኢንተርፕራይዞች የመስሪያ ቦታ ሼድ ቁልፍ ባዛሬው ዕለት አስረክቧል፡፡

ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ በተገኙበት በተደረገው የሼድ ርክክብ÷ በህገ-ወጥ መንገድ ተይዘው የነበሩና ከ5 ዓመት በላይ የሆናቸውን ደግሞ የ3 ወርና የ5 ወር ማስጠንቀቂያ ከተሰጣቸው በሗላ እንዲለቁ መደረጋቸው ተገልጿል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የስራ፣ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ ÷ የመስሪያ ቦታ ችግር በሆነበት ክፍለ ከተማ ያለችውን ውስን ቦታ በፍትሃዊነት ለማከፋፈል ለተደረገው ጥረት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የክፍለ ከተማው ምክትል ስራ አስፈፃሚና የስራ፣ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ጽህፈት ቤት ሃላፊ ወይዘሮ እመቤት ተስፋዬ ÷ በክፍለ ከተማው ለሚገኙ 65 ኢንተርፕራይዞችና 283 አንቀሳቃሾች የመስሪያ ቦታ ቁልፍ ርክክብ መደረጉን ገልፀዋል፡፡

የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሮ ሽታዬ መሃመድ በበኩላቸው የስራ እድል ፈጠራ ላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመው÷ ሼድ ያገኙ አንቀሳቃሾችም ለትክክለኛው አላማ እንዲያውሉ ማሳሰባቸውን ከክፍለ ከተማው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.