Fana: At a Speed of Life!

ሞሮኮ እና ክሮሺያ ጥሎ ማለፉን ተቀላቀሉ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 22፣ 2015 (ኤፍቢ ሲ) አፍሪካዊቷ ሀገር ሞሮኮ ካናዳን 2 ለ 1 በማሸነፍ እና ክሮሺያ ያለምንም ግብ ከቤልጂየም ጋር አቻ በመለያየት ጥሎ ማለፉን ተቀላቅለዋል፡፡

ሞሮኮ ከምድቧ 7 ነጥብ በመያዝ በቀዳሚነት እንዲሁም ክሮሺያ ደግሞ አምስት ነጥብ በመያዝ ነው ጥሎ ማለፉን የተቀላቀሉት፡፡

በኳታር አስተናጋጅነት እየተካሔደ በሚገኘው 22ኛው የዓለም ዋንጫ በምድብ ሥድስት የተደለደሉት ሞሮኮ እና ካናዳ ምሽቱን ጨዋታቸውን አካሂደዋል፡፡

በዚሁ መሠረት ሞሮኮ ካናዳን 2 ለ1 በመርታት ከሴኔጋል በመቀጠል ጥሎ ማለፉን የተቀላቀለች ሁለተኛዋ አፍሪካዊት ሀገር ሆናለች፡፡

በተመሳሳይ በዚሁ ምድብ የሚገኙት ክሮሺያ እና ቤልጂየም ያደረጉት ጨዋታ÷ ያለምንም ጎል በአቻ ውጤት መጠናቀቁን ተከትሎ ክሮሺያ ጥሎ ማለፉን ተቀላቅላለች፡፡

የሞሮኮን ጎሎች ሃኪም ዛይች በ4ኛው እና ዩሱፍ ኢን ነስሪ በ23ኛው እንዲሁም የካናዳን ብቸኛ ጎል ደግሞ ነይፍ አጉየርድ በ40 ኛው ደቂቃ አስቆጥረዋል፡፡

እስካሁን ድረስ÷ ኔዘርላንድስ፣ አሜሪካ፣ አርጀንቲና፣ አውስትራሊያ፣ ፈረንሳይ፣ ፖላንድ፣ እንግሊዝ፣ ሴኔጋል፣ ሞሮኮ እና ክሮሺያ ጥሎ ማለፉን የተቀላቀሉ ሀገራት ናቸው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.