Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ 60 የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታዎች መጠናቀቃቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በከተማዋ የሚስተዋለውን የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታዎች ችግር ለመቅረፍ 60 የስፖርት ማዘውተሪያ በታዎች መጠናቀቃቸው የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ስፖርት ምክር ቤት 13ኛ መደበኛ ጉባዔ ተካሂዷል፡፡

የምክር ቤቱ ሰብሳቢ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንደገለጹት÷ እንደከተማ ስፖርቱ በሚፈለገው ልክ ላለማደጉ እንደምክንያት የሚነሳው እና ባለፉት ዓመታት ተጠይቆ መፍትሄ ያልተገኘለት ደረጃውን የጠበቀ የስፖርት ማዕከል ግንባታ ጉዳይ ምላሽ አግኝቷል፡፡

ለግንባታው የሚሆን ዝግጅት በመጠናቀቅ ላይ መሆኑን ጠቁመው÷ የስፖርት ማዕከል ግንባታው በቀጣይ በጀት ዓመት ይጀመራል ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል በከተማዋ የሚስተዋለውን የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታዎች ችግር ለመቅረፍ 60 የስፖርት ማዘውተሪያ በታዎች ተጠናቀዋል ማለታቸውን የከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

የከተማውን ፕላን በጠበቀ መልኩ ቦታዎቹን የማዘጋጀት ስራ ቀጣይነት ይኖረዋል ብለዋል።

ስፖርት የኢትዮጵያን ገፅታ የመቀየር ትልቅ ኃይል ስላለው በዓለም አቀፍ መድረክ ሀገራቸውን መወከል የሚችሉ ስፖርተኞችን ለማፍራት በትኩረት እንደሚሠራ አመላክተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.