Fana: At a Speed of Life!

886 የሞባይል ቀፎዎችን በሕገ ወጥ መንገድ ሲያዘዋውር የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 886 የሞባይል ቀፎዎችን (አፓራተሶችን) በሕገ ወጥ መንገድ ወደ አዲስ አበባ ሊያስገባ የነበረ ተጠርጣሪ የብሔራዊ መረጃና ደኀንነት አገልግሎት ከኦሮሚያ ፖሊስ ጋር ባደረጉት ክትትል በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡

ተጠርጣሪው መነሻውን ጉጂ ነገሌ መዳረሻውን አዲስ አበባ በማድረግ በሕገወጥ መንገድ የሞባይል ቀፎ በማዘዋወር ላይ ሳለ በቁጥጥር ስር መዋሉን ምንጮች ጠቁመዋል፡፡

ግለሰቡ 886 የሞባይል ቀፎዎችን (አፓራተሶችን) ይዞ ከሞጆ ቢሾፍቱ ከዚያ በሰንዳፋ ወደ አዲስ አበባ ለመግባት ሲሞክር የብሔራዊ መረጃና ደኀንነት አገልግሎት ከኦሮሚያ ፖሊስ ጋር በቅንጅት ባደረጉት ክትትል በቁጥጥር ስር መዋሉን ምንጮች አመላክተዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.