Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ ለተባበሩት ዓረብ ኢምሬቶች ብሔራዊ ቀን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበበ፣ ሕዳር 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለተባበሩት ዓረብ ኢምሬቶች ብሔራዊ ቀን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
 
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷”ለወንድሜ እና ጓደኛዬ የተባበሩት ዓረብ ኢምሬቶች ልዑል አልጋ ወራሽ ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ አል ነህያን እንኳን ለ51ኛው የብሔራዊ ቀን አደረሳችሁ” ብለዋል፡፡
 
በተጨማሪም ለተከበረው የተባበሩት ዓረብ ኢምሬቶች ሕዝብ እንኳን ለ51ኛው የብሔራዊ ቀን አደረሳችሁ ሲሉ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.