Fana: At a Speed of Life!

በዛሬው የዓለም ዋንጫ ሁለት የአፍሪካ ሀገራት የሚሳተፉበትን ጨምሮ አራት ጨዋታዎች ይካሔዳሉ

አዲስ አበበ፣ ሕዳር 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ22ኛው የዓለም ዋንጫ ዛሬ ከምድብ ሰባት እና ስምንት ወደ ጥሎ ማለፍ የሚቀላቀሉ ቡድኖችን ለመለየት የሚደረጉ ጨዋታዎች ይከናወናሉ፡፡

በዚሁ መሰረት በምድብ ሰባት የተደለደለችው ብራዚል ቀድማ ጥሎ ማለፉን መቀላቀሏን ብታረጋግጥም የምድቧን ሶስተኛ ጨዋታ ከአፍሪካዊቷ ካሜሮን ጋር ምሽት አራት ሰዓት ላይ ታደርጋለች፡፡

በዚሁ ምድብ በተመሳሳይ ሰዓት ሰርቢያ እና ስዊዘርላንድ ጨዋታቸውን የሚያከናውኑ ይሆናል፡፡

በሌላ የጨዋታ መርሐ ግብር በምድብ ስምንት የሚገኙት ጋና እና ኡራጋይ ምሽት 12 ሰዓት ላይ ይፋለማሉ፡፡

በዚሁ ምድብ በተመሳሳይ ሰዓት ፖርቹጋል ቀድማ ጥሎ ማለፉን መቀላቀሏን ብታረጋግጥም ከደቡብ ኮሪያ ጋር ጨዋታዋን ታደርጋለች፡፡

በ22ኛው የኳታር የዓለም ዋንጫ እስካሁን አስራ ሁለት ቡድኖች ጥሎ ማለፉን መቀላቀላቸውን አረጋግጠዋል፡፡

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.