Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል በጦርነቱ የወደሙ ተቋማት መልሶ ግንባታና የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል በጦርነት የወደሙ ተቋማት ግንባታ እና የገቢ ማሰባሰቢያ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በሰሜን ወሎ ዞን ራያ ቆቦ ወረዳ መካሄድ ጀምሯል።

በመርሐ ግብሩ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለን ጨምሮ የክልሉናየዞን አመራሮች፣ የሃይማኖት አባቶችና ሌሎች ባላድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

የአማራ ክልል በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎች መልሶ ማቋቋም ፈንድ ፅህፈት ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ ዶክተር አባተ ጌታሁን÷ የመልሶ ማቋቋም ግንባታውን ለማስጀመር የክልሉ መንግስት 1 ቢሊየን ብር በጀት መድቧል ብለዋል።

በዛሬው ዕለት በራያ ቆቦ ወረዳ ወርቄ ቀበሌ የአራት ፕሮጀክቶች ግንባታ የማስጀመር መርሐ ግብር እንደሚከናወን ተናግረዋል።

ከሚገነቡት ፕሮጀክቶች መካከልም ትምህርት ቤት፣ የጤና ጣቢያ፣ የእንስሳት ጤና ክሊኒክና የግብርና ተቋማት እንደሚገኙበት ተገልጿል፡፡

ተመሳሳይ መርሐ-ግብር በጦርነቱ ጉዳት በደረሰባቸው ሁሉም ዞኖች እንደሚካሄድ መገለጹን ከሰሜን ወሎ ዞን ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.