Fana: At a Speed of Life!

ጋዜጠኛ ሽፈራው ታደለ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ 

አዲስ አበበ፣ ሕዳር 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞው የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋዜጠኛ ሽፈራው ታደለ ባጋጠመው ድገተኛ ህመም ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ ፡፡

ጋዜጠኛ ሽፈራው ከእናቱ ከወ/ሮ ፅጌ ሽፈራ እና ከአባቱ አቶ ታደለ ጉልማ በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ዳዎ ወረዳ በኡልማ ቡሳ ቀበሌ በጥቅምት 14 ቀን 1975 ዓ.ም ነው የተወለደው።

የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን በቡሳ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በህብረት ፍሬ ት/ቤት የተማረ ሲሆን በ1997 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ የመጀመሪያ ድግሪውን እንዲሁም ሁለተኛ ድግሪውን ደግሞ ከአርሲ ዩንቨርሲቲ በ2011 ዓ.ም አግኝቷል፡፡

ጋዜጠኛ ሽፈራው ታደለ በዳዎ ወረዳ ከመምህርነት ጀምሮ በተለያዩ ጽህፈት ቤቶች በኃላፊነት ደረጃ ያገለገለ ሲሆን በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በጋዜጠኝነት እና በተለያዩ ደረጃዎች ማገልገሉ አገልግሏል፡፡

ጋዜጠኛ ሽፈራው ከመስከረም ወር 2002 ዓ.ም ጀምሮ በኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔቶርክ ከአዘጋጅነት እስከ ዳሬክተርነት አገልግሏል።

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.