Fana: At a Speed of Life!

በመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮች አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሳቸው ተገለጸ

አዲስ አበበ፣ ሕዳር 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሁኑ ወቅት በመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮች እጅግ በጣም አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሳቸውን የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በአገልግሎት አሰጣጥ ችግር የሚታይባቸው የፌዴራል ተቋማትና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከሁሉም ክፍለ ከተሞች የሰው ሃብት ቢሮ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች እየተወያየ ነው፡፡

በውይይት መድረኩ በሀገራችን የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ እየታዩ ያሉ ችግሮች እጅግ በጣም አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሳቸው ተመላክቷል፡፡

በአሁኑ ወቅት የተሰጠን የስራ ሃላፊነት በመጠቀም የመንግስት አገልግሎትን በገንዘብ መሸጥ የተለመደ መሆኑም ነው የተገለጸው፡፡

በምክክር መድረኩ ከዚህ ችግር ፈጥኖ ለመውጣት መደረግ ባለባቸው ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት እንደሚደረግ የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

በመድረኩ አገልግሎት አሰጣጣችን ምን ይመስላል? በተገልጋዮች ቅሬታና አቤቱታ ማስተናገጃ መመሪያ እንዲሁም አገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያ ሥራዎች ዙሪያ ሰፊ ውይይት እንደሚካሄድም ተጠቁሟል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.