Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደስታ ሌዳሞ በኢትዮጵያ የአሜሪካ መንግሥት ጉዳይ ፈፃሚ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበበ፣ ሕዳር 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ደስታ ሌዳሞ በኢትዮጵያ የአሜሪካ መንግሥት ጉዳይ ፈፃሚ ከሆኑት አምባሳደር ትሬሲ አን ጃኮብሰን ጋር ተወያዩ፡፡

በውይይቱ ላይ ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ባደረጉት ገለጻ÷ የአጎዋ ዕድል በመቋረጡ በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ የሚሠሩ ሠራተኞች ከሥራ ገበታቸው ውጭ መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡

አምባሳደር ትሬሲ አን ጃኮብሰን ፓርኩን በመጎብኘት እውነታውን እንዲገነዘቡ እና አሜሪካም ጉዳዩን ድጋሚ እንድታጤነው የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ አቶ ደስታ ጠይቀዋል፡፡

የአሜሪካ መንግሥት በልማት ድርጅቶቹ በኩል እያደረገ ላለው ድጋፍ ያመሰገኑት አቶ ደስታ÷ ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

አምባሳደር ትሬሲ አን ጃኮብሰን በበኩላቸው የልማት ትብብሩ ተጠናክሮ ይቀጥላል ማለታቸውን የርዕሰ መስተዳድር ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

የአጎዋ ዕድልንም መልሶ ለማየት በአሜሪካ መንግሥት በኩል ሥራዎች እየተሠሩ ነው ብለዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.