Fana: At a Speed of Life!

1ሺህ 214 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በዛሬው እለት በሶስት ዙር በተከናወነ በሳዑዲ አረቢያ በችግር ያሉ ዜጎችን የመመለስ ስራ 1ሺህ 214 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለስ መቻሉ ተገለፀ፡፡

ከመለሱት ዜጎች መካከል 774 ወንዶች፣ 220 ሴቶች እና 220 ህፃናትና እድሜያቸው ከ18 አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ናቸው ተብሏል፡፡

ለተመላሽ ዜጎች ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማእከላት እንዲሄዱ መደረጉን ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከህዳር 12 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን በተከናወነ ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ 6 ሺህ 881 ኢትዮጵያውያንን መመለስ መቻሉ ተመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.