Fana: At a Speed of Life!

17ኛው ዓለም አቀፍ የበይነ-መረብ አስተዳደር ጉባኤ ተጠናቀቀ

አዲስ አበበ፣ ሕዳር 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ያስተናገደችው 17ኛው ዓለም አቀፍ የበይነ-መረብ አስተዳደር ጉባኤ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል።

በመዝጊያ ዝግጅቱ ላይ የተገኙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጉባኤው የተሳካ እንዲሆን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና አጋሮች ላደረጉትን ጥረት አመስግነዋል።

ኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚ ለመገንባት እየሰራች መሆኑን ያነሱት አቶ ደመቀ በጉባኤው የተነሱ ሃሳቦች ወደ ውጤት እንዲቀየሩ ጉባኤው ክትትል ያደርጋል የሚል እምነት እንዳላቸው ገልፀዋል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ምክትል ዋና ፀሃፊ ሊ ጁንሁዋ በቪዲዮ ባስተላለፉት መልዕክት ከበይነመረብ አስተዳደር ጋር የተያያዙ ችግሮችን ለመፍታት በጋራ መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢኮኖሚና ማህበራዊ ጉዳዮች ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ፔድሮ መድረኩ ከፍተኛ የአፍሪካውያን ተሳትፎ የታየበት መሆኑን አንስተዋል፡፡

የአፍሪካ ድምፅ ተሰሚ እንዲሆን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢኮኖሚና ማህበራዊ ጉዳዮች በትኩረት እንደሚሰራ ዋና ፀሃፊው ማረጋገጣቸውን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.