Fana: At a Speed of Life!

በዓለም ዋንጫው ሩብ ፍጻሜውን ለመቀላቀል ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ይደረጋሉ

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 24 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም ዋንጫው የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ዛሬ ይጀመራሉ።

ኔዘርላንድስ ከአሜሪካ እንዲሁም አርጀንቲና ከአውስትራሊያ የዛሬ ጥሎ ማለፍ መርሐ ግብሮች ናቸው።

ቀድም ብሎ በሚካሄደው ጨዋታ ምድብ 1ን በቀዳሚነት የጨረሰችው ኔዘርላንድስ ከምድብ 2 ሁለተኛ በመሆን ካጠናቀቀችው አሜሪካ ጋር ሩብ ፍጻሜውን ለመቀላቀል ትጫወታለች።

የምድብ ሶስቷ አርጀንቲና ደግሞ በምድብ አራት ፈረንሳይን ተከትላ ካለፈችው አውስትራሊያ ጋር ትገናኛለች።

የሁለቱ ጨዋታ አሸናፊዎች ሕዳር 30 ቀን ግማሽ ፍጻሜውን ለመቀላቀል ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.