Fana: At a Speed of Life!

ወጋገን ባንክ ከታክስ በፊት ከግማሽ ቢሊየን ብር በላይ አተረፈ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ወጋገን ባንክ ከታክስ በፊት 572 ሚሊየን ብር ትርፍ ማስመዝገቡን አስታውቋል፡፡

ባንኩ የባለአክሲዮኖች 29ኛ መደበኛ እና14ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ አካሂዷል፡፡

በጉባዔው ላይ እንደተገለጸው÷ እያንዳንዱ አክሲዮን ያስገኘው ትርፍ ወደ 16 ነጥብ 6 በመቶ አድጓል፡፡

ባንኩ ከነበረበት የአፈጻጸም መቀነስ ወጥቶ በ2021/2022 ወደትርፋማነት መመለስ መቻሉን የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አብድሹ ሁሴን ተናግረዋል፡፡

በትግራይ ክልል የሚገኙ 112 የባንኩ ቅርንጫፎች አገልግሎት ሳይሰጡ በሌሎች አካባቢዎች በሚገኙ 288 ቅርንጫፎች ብቻ እየሠራ ይህን ውጤት ማስመዝገቡ አበረታች ነው ብለዋል፡፡

የባንኩ ጠቅላላ ሀብት በተጠናቀቀው ዓመት 43 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር መድረሱ ተመላክቷል።

የባላክሲዮኖች ቁጥር ከ7 ሺህ በላይ መድረሱ ተገልጿል፡፡

በቅድስት ብርሃኑ

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.