Fana: At a Speed of Life!

በሲዳማ ክልል ዘንድሮ ከ283 ሺህ ቶን በላይ ቡና ለገበያ ለማቅረብ እየተሠራ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሲዳማ ክልል በተያዘው በጀት ዓመት ከ283 ሺህ ቶን በላይ ጥራቱን የጠበቀና የታጠበ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ፡፡

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር  ደስታ ሌዳሞ እንደገለጹት÷ በሲዳማ ክልል የቡና ማሳን በማስፋትና ምርታማነትን በማሳደግ የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተሠራ ነው፡፡

በክልሉ 160 ሺህ ሔክታር በቡና ተክል መሸፈኑን እና የተሻለ ምርት የሚሰጡ ዝርያዎችን በመትከል የአርሶ አደሩን ኑሮ ለመለወጥ እየተከናወኑ ያሉት ተግባራት አበረታታች መሆናቸውን ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡

የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ መስፍን ቃሬ ዘንድሮ በክልሉ 1 ነጥብ 3 ሚሊየን ኩንታል የቡና ምርት እንደሚሰበሰብ ይጠበቃል ብለዋል፡፡

283 ሺህ ቶን የታጠበ እሸት ቡናና 40 ሺህ ቶን ደረቅ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል።

ከሁለት ሔክታር በላይ የቡና ማሳ ያላቸው አርሶ አደሮች በቀጥታ ለውጪ ገበያ ለማቅረብ የተሰጣቸውን ዕድል ለመጠቀም ዘንድሮ ፈቃድ እንደሚያወጡ ተገልጿል፡፡

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.