Fana: At a Speed of Life!

የብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀንን ምክንያት በማድረግ በመዲናዋ የባህል ፌስቲቫል እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 25 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)17ኛው የብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀንን ምክንያት በማድረግ “ህብረ ብሄራዊ አንድነታችን ለዘላቂ ሰላማችን” በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ የባህል ፌስቲቫል እየተካሄደ ነው።

በባህል ፌስቲቫሉ ላይ ሁሉንም ብሄር ብሄረሰቦች የሚወክሉ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል።

የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች የባህል ምግቦች፣ አልባሳት እና ባህላዊ ውዝዋዜዎችም እየቀረቡ ነው።

በፌስቲቫሉ ላይ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የመዲናዋ ነዋሪዎች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው ታዳሚዎች መገኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

17ኛው የብሄር በሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ የፊታችን ሀሙስ ህዳር 29 ቀን 2015ዓ.ም በሲዳማ ክልል ሀዋሳ ከተማ ይከበራል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.