Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል ከ500 ሺህ ሄክታር መሬት በላይ በዘር ተሸፍኗል-የክልሉ ግብርና ቢሮ

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 25 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)በኦሮሚያ ክልል በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ከ500 ሺህ ሄክታር መሬት በላይ በዘር መሸፈኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ ገልጿል፡፡

በክልሉ የበጋ መስኖ ስንዴን በዘር የመሸፈን ስራ ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን÷በክልሉ በጋ መስኖ ስንዴ በዘር መሸፈን እና የመኸር ምርት ስብሰባ ያለበት ደረጃ ተቃኝቷል።

በዚህም የኦሮሚያ ግብርና ቢሮ ሃላፊ ጌቱ ገመቹ እና የሴክተሩ የስራ ሃላፊዎች በአርሲ ዞን ዶዶታ ወረዳ በክላስተር የተዘጋጀ የስንዴ ማሳን በዘር የመሸፈን ስራ ጎብኝተዋል።

በክልሉ በበጋ መስኖ ስንዴ 1 ሚሊየን ሄክታር በዘር ለመሸፈን ታቅዶ እስካሁን ከ700 ሺህ በላይ ማሳ መዘጋጀቱን እና ከ500 ሺህ ሄክታር መሬት በላይ ደግሞ በዘር መሸፈኑን ሃላፊው ገልፀዋል።

በቀሪ አንድ ወር በሚጠጋ ጊዜ ውስጥም ቀሪውን ለመሸፈን እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።

በአርሲ ዞን ደግሞ 100 ሺህ ሄክታር በዘር ለመሸፈን የታቀደ ሲሆን÷ እስካሁን 46 ሺህ የሚሆነው በዘር ተሸፍኗል ነው የተባለው።

በሀብታሙ ተ/ስላሴ

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.