Fana: At a Speed of Life!

አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ በቀድሞው የቻይና ፕሬዚዳንት ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ በቀድሞው የቻይና ፕሬዚዳንት ጂያንግ ዜሚን ህልፈት የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን ገልጸዋል፡፡

አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲ በመገኘት ነው በቀድሞው የቻይና ፕሬዚዳንት ጂያንግ ዜሚን ህልፈት የተሰማቸውን ሐዘን ለቻይና መንግስት እና ሕዝብ የገለጹት፡፡

አፈጉባኤው የቀድሞው ፕሬዚዳንት ጂያንግ ዜሚን ለዓለም አቀፍ ሰላም እና መረጋጋት ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረከቱ የቻይና  መሪ  እንደነበሩ  አውስተዋል፡፡

አቶ ታገሰ ለቻይና ሕዝብ እና  መንግስት እንዲሁም ለሟች ቤተሰቦች መጽናናትን መመኘታቸውንም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የቀድሞው የቻይና ፕሬዚዳንት ጂያንግ ዜሚን በሳለፍነው ሕዳር 21 ቀን 2015 ዓ.ም ከደም ካንሰር ጋር በተያያዘ በደረሰባቸው ፅኑ ሕመም በተወለዱ በ96 ዓመታቸው ሕይወታቸው ማለፉ ይታወሳል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.